Watch #ዝምአልልም ሁለተኛውን ምዕራፍ እንቅስቃሴ ጀምረናል!!!! እንቅስቃሴውን ይቀላቀሉ!!! on All Habesha
Petition link :-
ወንዶችና ሴቶች ህጻናት በመደፈር ከሚደርስባቸው የሰዕብና ስብራት በጠንካራ የሕግ ማዕቀፍና አፈፃፀም እንዲጠበቁልኝ እዚህ ቅፅ ላይ በመፈረም አቤቱታዬን ለመንግስት አቀርባለሁ! ይህንን ቅፅ ስፈርም አስገድዶ መድፈርና ወሲባዊ ጥቃት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን በመገንዘብ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስትን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀፆችን፤አንቀፅ 620(1)፣ አንቀፅ 620(2)(ሀ)፣ አንቀፅ 620(3)፣ አንቀፅ 626 (1) እና(4ሀ) እንዲያሻሻል እጠይቃለሁ።
በዚህምመሰረት፣
* ሴቶች ላይ ለሚደርሱ የመደፈርና ወሲባዊ ጥቃቶች የጣለው የእስራት ቅጣት ከፍ ብሎ ከ20 ዓመት ፅኑ እስራት በመጀመር እስከ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት ከፍ እንዲደረግና የገንዘብ ቅጣትንም እንዲያካትት እጠይቃለሁ።
* ጥቃቱ በሴትና ወንድ ህፃናት ላይ በደረሰ ጊዜ የጣለው የእስራት ቅጣት ከፍ ብሎ ከእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እስከሞት በሚደርስ እንዲያስቀጣ ማሻሻያ እንዲደረግበት እጠይቃለሁ።
AllHabesha is where all Habeshas meet.